SWE-RDRMC – Southern Ethiopia Disaster Risk Reduction Management Commission
Sep 4, 2026
የአደጋ ስጋት ቅድመ ዝግጅት እና ዕቅድ ላይ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ

የክልሉ አደጋ ስጋት ኮሚሽን ከአውሮፓ ሕብረት ጋር በመተባበር በተርጫ ከተማ ለ44 ባለሙያዎች በፖሊሲ፣ አውቶሜሽን እና ዕቅድ ዙሪያ የአንድ ቀን የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጥቷል።

በስልጠናው ከዳውሮ ዞን ጌና፣ ማሪ ማንሳ እና እሰራ ወረዳዎች፣ ከኮንታ ዞን አሜያ ዙሪያ እንዲሁም ከትምህርት፣ ጤና፣ ውሃ፣ ግብርና፣ ሴቶችና ሕፃናት፣ አስተዳደር እና አደጋ ስጋት ዘርፎች የተውጣጡ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የኮሚሽኑ ቅ/ማ/ም ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ከስልጠናው በኋላ ከተሳታፊዎች ብዙ ሥራ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል።

በተለይም የአደጋ ስጋት ቅድመ ዝግጅትና መከላከያ ሥራዎች ከመደበኛ የሥራ እቅድ ጋር በማቀናጀት መስራት እንደሚገባ አፅንዖት ሰጥተዋል። ተሳታፊዎችም ከስልጠናው ያገኙትን እውቀትና ክህሎት በሥራቸው ላይ በተግባር እንዲያውሉ መመሪያ ሰጥተዋል።

ስልጠናው የአደጋ ስጋትን በቅድሚያ ለመለየት፣ ለመከላከል እና የተቀናጀ ዕቅድ በማዘጋጀት የተሻለ የአደጋ ስጋት አስተዳደር ሥርዓት ለመገንባት የሚያግዝ መሆኑ ተገልጿል።

More Details
Sep 4, 2026
EU DDRM Training Workshop